አማርኛ

አማርኛ : SPL Hotspot - ማወቅ የሚያስፈልገኝ ምንድን ነው?

用拼音检索馆藏中文书刊资料

活动一览表 作者朗读会、课程、活动和为成年人安排的特别文化节目。

查找图书馆馆址


图书馆方位图

SPL Hotspot - ማወቅ የሚያስፈልገኝ ምንድን ነው?

SPL HotSpot - Connecting Seattle

Wi-fi hotspot

መመሪያዎች:

 1. ይህን፤ ይጫኑና ይቆዩ ማብሪያ፣ ማጥፊያ። የኤሌክትሪክ መሰኪያ ገመዱን መጠቀም አያስፈልግዎትም – የሚያገለግለው መሣሪያውን ባትሪ ለመሙያ ነው።
 2. መሣሪያውን ጥቂት ስክሪን እስከሚለዋውጥ ድረስ በግምት 30 ሰኮንዶች ይጠብቁ።
 3. የ"የእንኳን ደህና መጡ ማስተዋወቂያ" ለማየት መምረጫቁልፍ መጫን ሊያስፈልግዎ ይችላል።
   
  ማሳሰቢያ፦ ስክሪኑ ባዶ ከሆነ፣ ማብሪያ፣ ማጥፊያ ቁልፉን ለአጭር ጊዜ በመጫን እንደገና ይክፈቱት። (ተጭነውት አይቆዩ።)
 4. ስክሪኑ ከታች በኩል “Wi-Fi ስምና ፓስወርድ” የሚል ጽሑፍ ሲያሳይ፤ የ መምረጫ ቁልፍ ይጫኑ። የሆት ስፖት ስምና ፓስወርድ በስክሪኑ ላይ ይታያል።
 5. የኮምፒውተርዎ ወይም የመሣሪያዎ Wi-Fi ማስተካከያ ላይ የ HotSpot ስም ይምረጡና የሆትስፖት ፓስወርድ ያስገቡ።

 

ጠቃሚ መረጃዎች:

 1. ይፈላልጉ፦ የተለያዩ ስክሪኖችን ለማየት ከመሣሪያው በስተግርጌ ያሉትን ቁልፎች በቀስታ ነካ ያድርጉ። ይህ መሣሪያ የሚነካ ስክሪን (ታች ስክሪን) የለውም።
 2. መሣሪያውን እንደ አዲስ ማስነሳት፦ ችግር ካጋጠመዎት፣ እንደ አዲስ ለማስነሳት፤በወረቀት አግራፍ (ክሊፕ) የ እንደ አዲስ ማስነሻ ቁልፍን ይጫኑ። እንደ አዲስ ማስነሻ ቁልፍ አነስተኛ ጎድጓዳ የአራት ማዕዘን ሲሆን ከጀርባ መሸፈኛው ሥር “reset” የሚል ጽሑፍ አለው።

የመጠቀሚያ ማሳሰቢያዎች፦

 • ውስጣዊ መልእክት፦ ይህ መሣሪያ ውስጣዊ መልዕክትን መርጦ አያሳይም። ወላጆችና ሞግዚቶች የልጆችን በኢንተርኔት የሚያደርጉትን ተግባር የመቆጣጠር ኃላፊነት አለባቸው።
 • HotSpot እስከ 15 የሚሆኑ በ Wi-Fi መሥራት የሚችሉ መሣሪያዎችን ያገናኛል።
 • ክፍያ ሂሳብ፦ ለጠፉ መሣሪያዎች ወይም ለተበላሹ መሣሪያዎች $199 ክፍያ በቤተ መጻሕፍት ሂሳብዎ ላይ እንዲከፍሉ ይሆናል።
 • ቀኑ ካለፈ፦ ቀኑ ካለፈበት የመጨረሻ ጊዜ 24 ሰዓት በኋላ የኢንተርኔት መሥመሩ እንዲቋረጥ ይደረጋል።
 • የመሣሪያውን ባትሪ ለመሙላት ለሞምላት፦ እባክዎ መሣሪያውን ከመመለስዎ በፊት ባትሪውን በደንብ ይሙሉ። የኤሌክትሪክ ገመዱና ባለ-ሁለት ጣት ኤሌክትሪክ ማመንጫ ያስፈልግዎታል። ከመሣሪያው በስተጎን በኩል የሚገኘውን ተንሸራታች ሽፋን ይመልከቱ። HotSpot ከእርሶ ትይዩ ሆኖ፤ ሽፋኑን ወደ ግራ ያንሸራቱት። በማሳያው ላይ እንደሚታየው ያገናኙ። የባትሪ ማሳያ ስክሪን ባትሪው 100% ብሎ እስከሚያሳይ ድረስ ኤሌክትሪኩን ሰክተው ይቆዩ።

recharge hotspot

Get the User Guide
Ask a Librarian
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።